የ Thrive By 5 MoCo ሃብቶች
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ እድሜያቸው 5 ዓመት እስኪሞላ ድረስ ልጆችን የሚደግፉ የፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ዝርዝር ይፈልጉ። በልጅዎ ዕድሜ ወይም በሚፈልጉት የግብዓት/ሀብት አይነት ዝርዝሩን ለማየት ሙሉውን የሀብት ዝርዝር ይፈልጉ ወይም ከታች ያሉትን በተኖች ይጠቀሙ። በአንድ ጊዜ ብዙ የማጣሪያ መስፈርቶችን መምረጥ ወይም አለመምረጥ ይችላሉ። የማጣሪያ መስፈርቶችን እና ፍለጋዎን ድጋሚ ለማስጀመር፣ “ሁሉንም አጥፋ” የሚለውን በተን ይምረጡ።
ለሌሎች የአካባቢ ግብዓት አይነቶች፣ የ infoMONTGOMERY ማውጫን ይጎብኙ።
ስለ እኛ የግብዓት/ሀብት አይነቶች የበለጠ ለማወቅ እዚህ ጠቅ ላይ ያድርጉ ።
የልጅ ዕድሜ፦
የግብዓት/ሀብት አይነት፡

Babies Born Healthy
Babies Born Healthy በሞንትጎመሪ ካውንቲ ዳውንካውንት ክልል ውስጥ የሚኖሩ እና Medicaid የሚያገኙ ብቁ የሆኑ ጥቁር ወይም አፍሪካዊ አሜሪካዊ ነፍሰ ጡር ግለሰቦችን ይደግፋል። ቤተሰቦች የእንክብካቤ ቅንጅት፣ የቅድመ ወሊድ ትምህርት እና ጤናማ እርግዝናዎችን እና ጤናማ የልጆች ለመደገፍ ከሚረዱ ሀብቶች ጋር ግንኙነት ያገኛሉ።
በሚከተሉት ዚፕ ኮዶች ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች ብቁ ናቸው፦ 20903፣ 20904 እና 20906

Care for Kids
Care for Kids በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ኢንሹራንስ ለሌላቸው ልጆች የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን የሚሰጥ የጤና እንክብካቤ ፕሮግራም ነው። የልጆች እንክብካቤ የጤናማ ልጆች ጉብኝቶችን፣ የህመም ጊዜ ጉብኝቶችን፣ የታዘዙ መድሃኒቶችን፣ የዓይን ምርመራን፣ የጥርስ ህክምና እና ሌሎች ውስን የልዩ እንክብካቤ አገልግሎቶችን ያካትታል።
ብቁነት፡
- ልጁ የመድህን ዋስትና የሌለው መሆን አለበት
- ልጁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ መሆን አለበት
- ዕድሜ አዲስ ከተወለዱ ልጆች እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ያላቸው
- የቤተሰብ ገቢ ከፌዴራል የድህነት ደረጃ 250% መብለጥ የለበትም

የልጆች እንክብካቤ ስኮላርሺፕ (CCS)
የልጆች እንክብካቤ ስኮላርሺፕ (CCS) ፕሮግራም በሜሪላንድ ውስጥ በገቢያቸው መሰረት ብቁ የሆኑ ቤተሰቦች ከፍተኛ ጥራት ላለው የልጆች እንክብካቤ እና የቅድመ እንክብካቤ እና የትምህርት ፕሮግራሞች መክፈል እንዲችልይ ይረዳል። አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ፣ የስኮላርሺፕ ክፍያዎች በቀጥታ ብቁ ለሆነ የልጆች እንክብካቤ አቅራቢ ይከፈላሉ።
ልዩ ማሳሰቢያ፡- ከግንቦት 2025 ጀምሮ የልጆች እንክብካቤ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም የምዝገባ እገዳን አቋቁሞ ፍላጎት ያላቸውን ቤተሰቦች የተጠባባቂ ዝርዝር ፈጥሯል። አንዳንድ ቤተሰቦች እገዳው አይጣልባቸውም። አዲስ ቤተሰቦች ከተጠባባቂ ዝርዝሩ ውስጥ አገልግሎት እያገኙ ስለሆነ ቤተሰቦች አሁንም ማመልከት አለባቸው። ስለ ምዝገባ እገዳው የበለጠ እዚህ ላይ ይወቁ።
ብቁነት፡
- እድሜው ከ13 ዓመት በታች የሆነ ልጅ፣ ወይም
- ብቁ የሆነ የአካል ጉዳት ያለበት እድሜው ከ13-19 ዓመት የሆነ ግለሰብ።
- የሜሪላንድ ነዋሪ የሆነ፣ በተፈቀደ የሥልጠና ፕሮግራም ውስጥ የሚሰራተቀጣሪ የሆነ፣ ወይም ተማሪ የሆነ። ሁለቱም ወላጆች በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩባቸው ቤተሰቦች፣ ሁለቱም ወላጆች ሁሉንም የብቁነት መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ጊዜያዊ የገንዘብ ድጋፍ (TCA) ወይም ተጨማሪ የደህንነት ገቢ (SSI) ወይም በ CCS የገቢ መመሪያዎች ውስጥ የሚያገኙ።
- ልጅዎ በሜሪላንድ ግዛት ደረጃዎች መሰረት ክትባት እንዲወስድ ወይም ከክትባት ነጻ መሆንን የሚደግፍ ሰነድ ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን።
- የልጅ እንክብካቤ የሚያስፈልገው እያንዳንዱ ልጅ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ መሆኑን ወይም ብቁ የውጭ ዜጋ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ። (ለእያንዳንዱ ልጅ የልደት የምስክር ወረቀት ወይም የልጁን ሁኔታ የሚያረጋግጥ ሰነድ ያቅርቡ።) ማሳሰቢያ፡ ወላጆች የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ መሆን አይጠበቅባቸውም ።
- በቤተሰብ ስብጥር ውስጥ ላሉ አባላት በሙሉ የማንነት ማረጋገጫ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ። (የወላጅ የማንነት ማረጋገጫ በመንግስት የተሰጠ ማንኛውም ሰነድ ሊሆን ይችላል። የልደት የምስክር ወረቀት ወይም የስደተኝነት ሁኔታ ሰነዱ በቤተሰብ ስብጥር ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ልጅ የማንነት ማረጋገጫ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።)
- ፎቶ ያለው መታወቂያ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ (ከቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ብቻ የሚፈለግ)።

የልጆች እንክብካቤ ድጋፍ አገልግሎቶች
የቤተሰብ ድጋፍ አካል የሆነው የልጆች እንክብካቤ ድጋፍ አገልግሎቶች የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ ፕሮግራም ሲሆን፣ ቤተሰቦች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ካሉ ቤተሰብ እና ልጆች ተኮር ከሆኑ ሀብቶች ጋር እንዲገናኙ ለማገዝ የግል ምክክር ለማቅረብ ባለብዙ ቋንቋ የቤተሰብ ሀብት ባለሙያዎችን ይጠቀማል።
ከልጆት እንክብካቤ የድጋፍ አገልግሎቶች በተጨማሪ- የቤተሰብ ድጋፍ፣ የቅድመ ልጅነት አገልግሎቶች ከውልደት እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ድረስ ልጆችን እና ቤተሰቦችን የሚደግፉ በርካታ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። የበለጠ ለማወቅ ከታች ያሉትን ፕሮግራሞች ይመልከቱ፡

Child Find
Child Find ከ3 ዓመት እስከ መዋዕለ ህጻናት እድሜ ላሉ ልጆች ነጻ የእድገት ምርመራዎችን ያቀርባል።

EquiCare
የEquiCare Grant በገቢያቸው መሰረት ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች ለጨቅላ ህጻናት እና ለታዳጊ ህጻናት ነጻ የልጆች እንክብካቤ አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ድጋፍ በተሳታፊ የልጆች እንክብካቤ ፕሮግራሞች ላይ ይገኛል።
ብቁነት፡
- የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ የሆኑ
- የልጃቸው ዕድሜ ከ6 ሳምንት እስከ 4 ዓመት ዕድሜ የሆነ
- የገቢ መመሪያዎችን የሚያሟሉ
- በአሁኑ ጊዜ የስኮላርሺፕ ወይም የትምህርት ክፍያ ድጋፍ እያገኙ ያልሆኑ
- ለሜሪላንድ የህፃናት እንክብካቤ ስኮላርሺፕ (CCS) ፕሮግራም ወይም ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ስራ የሚሰሩ ወላጆች ድጋፍ (WPA) ድጋፍ ብቁ ያልሆኑ

የቤተሰብ ዲስከቨሪ ማዕከል በJSSA (Patty Center)
የቤተሰብ ዲስከቨሪ ማዕከል ለነፍሰ ጡር ሴቶች እና እስከ 4 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች የአዋቂዎች የእንግሊዝኛ ትምህርት እና የልጆች እድገት ፕሮግራሞችን ያቀርባል። ወላጆች በእንግሊዝኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ (ESOL) ክፍል በሚሆኑበት ሰዓት ልጆች ይማራሉ እንዲሁም ይጫወታሉ።

የቤተሰብ ተሳትፎ ማዕከል
የቤተሰብ ተሳትፎ ማዕከል (FIC) ማንኛውም ክህሎት ላላቸው እድሜያቸው ከውልደት እስከ 5 ዓመት ድረስ ለሆኑ ልጆች በቅድመ ልጅነት ክፍል ውስጥ ነጻ ጨዋታ ያለው ፕሮግራም ነው። የFIC የወላጅ አስተማሪ ቡድን ከወላጆች እና ከተንከባካቢዎች ጋር በመተባበር የሁሉንም ልጆች እድገት እያሻሻለ የወላጅነት ጥንካሬዎችን ለመገንባት ጨዋታን ይጠቀማል።
ቦታዎች፡
- Rockville: 1401 Rockville Pike, 2nd Floor; Rockville, MD 20852
Gaithersburg: 18100 Washington Grove Lane; Gaithersburg, MD 20877- Silver Spring: 2450 Lyttonsville Road; Silver Spring, MD 20910

የታላቁ ዲሲ Diaper Bank
በታላቁ ዲሲ Diaper Bank በኩል የሚገኙ Diaper Need Hubs ቤተሰቦች ምግብ እና ዳይፐር በአንድ ቦታ የሚያገኙበት ቦታን የሚያቀርቡ የማህበረሰብ አጋሮችና መሰረታዊ የፍላጎት አቅራቢ ድርጅቶች ናቸው።

ሄድ ስታርት እና ኧርሊ ሄድ ስታርት
ሄድ ስታርት እና ኧርሊ ሄድ ስታርት ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች የህጻናትን እድገት እና የትምህርት ቤት ዝግጁነትን የሚደግፉ ነጻ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የቅድመ ትምህርት ፕሮግራሞችን ይሰጣሉ። ፕሮግራሞቹ እርጉዝ ለሆኑሴቶች እና ከውልደት እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ላሉ ልጆች የጤና፣ የአመጋገብ እና የቤተሰብ ድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የተለያዩ የሄድ ስታርት እና የኧርሊ ሄድ ስታርት አማራጮች ያሉ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው የተለያዩ የዕድሜ ክልሎችን እና የፕሮግራም ሞዴሎችን ያገለግላሉ።
- MCPS Head Start ብቁ ለሆኑ እድሜያቸው ለ4 ዓመት ለሆኑ ልጆች ነጻ የቅድመ ትምህርት ቤት ትምህርት ይሰጣል።
- CentroNía እና Easterseals ብቁ ለሆኑ እርጉዝ ሴቶች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ታዳጊ ልጆች (ከውልደት እስከ 3 ዓመት) የኧርሊ ሄድ ስታርት አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።
- የሞንትጎመሪ ካውንቲ ኧርሊ ሄድ ስታርት ማህበረሰብ ተኮር የልጆች እንክብካቤ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ብቁ ለሆኑ እና ከውልደት እስከ 3 ዓመት እድሜ ድረስ ለሚገኙ ልጆች የኧርሊ ሄድ ስታርት አገልግሎቶችን ይሰጣል።
- የሄድ ስታርት እና ኧርሊ ሄድ ስታርት አመልካች ቤተሰቦች በሞንትጎመሪ ካውንቲ እና በመላ አገሪቱ የሚገኙትን ሁሉንም የሄድ ስታርት እና ኧርሊ ሄድ ስታርት ፕሮግራሞችን መፈለግ እንዲቹ ይረዳል።

የሞንትጎመሪ ጤናማ ቤተሰቦች
የሞንትጎመሪ ጤናማ ቤተሰቦች (Healthy Families Montgomery) ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅ ለወለዱ ወላጆች በSheppard Pratt የሚሰጥ ነጻ፣ በፈቃደኝነት የሚሰጥ የቤት ጉብኝት ፕሮግራም ነው። ቤተሰቦች ከእርግዝና ጀምሮ ልጃቸው 3 ዓመት እስኪሞላው ድረስ የግል ድጋፍ፣ የልጅ አስተዳደግ ትምህርት እና ከማህበረሰብ ሀብቶች ጋር የማገናኘት አገልግሎት ያገኛሉ።

ሞንትጎመሪ ካውንቲ፣ MD ውስጥ የሚገኘው ኢማጂኔሽን ቤተ መጻሕፍት
ኢማጂኔሽን ቤተ መጻሕፍት (Imagination Librar) በተወሰኑ ዚፕ ኮዶች ውስጥ ለሚኖሩ እና እድሜያቸው ከውልደት ጀምሮ እስከ 5ኛ ዓመት ልደታቸው ድረስ ለሚገኙ ልጆች ነጻ መጻህፍት ይሰጣል። በየወሩ አዲስ መጽሐፍ በፖስታ የሚደርሳቸው ሲሆን፣ ይህም ልጆች የቤተሰብ ገቢ ምንም ይሁን ምን የራሳቸውን የግል ቤተ መጻሕፍት እንዲገነቡ ያስችላቸዋል።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ብቁ የሆኑ ዚፕ ኮዶች፡ 20850፣ 20851፣ 20876፣ 20877፣ 20886፣ 20879፣ 20895፣ 20901፣ 20902፣ 20903፣ 20904፣ 20906፣ 20910፣ እና 20912።

ለአደጋ ተጋላጭ ህጻን የቤት ጉብኝት
ለአደጋ ተጋላጭ ህጻን የቤት ጉብኝት ፕሮግራም (Infant at Risk Home Visiting Program) አዲስ የተወለዱ ህጻናት ያሏቸው እና የሕክምና ወይም ማኅበራዊ ፍላጎቶች ሊኖራቸው ለሚችል ቤተሰቦች የግል ድጋፍ ይሰጣል። የቤት ጎብኚዎች ቤተሰቦችን ከሀብቶች ጋር ያገናኛሉ፣ መመሪያ ይሰጣሉ፣ እንዲሁም የወላጆችንም ሆነ የልጆትን ጤና፣ እድገት እና ደህንነት ለመደገፍ ይረዳሉ።
ቤተሰቦች የሚከተሉት ካጋጠማቸው ሪፈር ሊደረጉ ይችላሉ፦
- ከፍተኛ አደጋ ያለው እርግዝና ወይም ልጅ መውለድ
- ያለጊዜው የተወለደ ህጻን ወይም ሲወለድ ክብደቱ በጣም ዝቅተኛ መሆን
- ውስን የሆነ ወይም ምንም የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ አለመኖር
- የአእምሮ ወይም የባህሪ ጤና ስጋቶች
- አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም ወይም የመልሶ ማቋቋም ፍላጎቶች
- የተረጋጋ መኖሪያ አለመኖር ወይም ቤት አልባነት
- በቅርብ አጋር የተፈጸመ ጥቃት
- ገና በአፍላ እድሜ ላይ የተከሰተ እርግዝና
- ከዚህ በፊት የተከሰተ የህጻን ልጅ ሞት ወይም ያለጊዜ መወለድ
- የወላጅን ወይም የህጻኑን ጤና እና ደህንነት ሊነኩ የሚችሉ ሌሎች ሁኔታዎች
የሚገኝ ድጋፍ፦
- በሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚደረጉ የቤት ጉብኝቶች
- የልጅ አስተዳደግ ትምህርት እና ድጋፍ
- ስለልጆች እድገት መመሪያ
- ከጤና እንክብካቤ እና ከማህበረሰብ ሀብቶች ጋር ግንኙነቶች
- ተጨማሪ ፍላጎቶች ላሏቸው ቤተሰቦች የእንክብካቤ ማስተባበር

LOCATE፡ Child Care
LOCATE፡ Child Care ቤተሰቦች ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ቁጥጥር የሚደረግባቸው እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የልጆች እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያግዝ የሜሪላንድ የቤተሰብ ኔትወርክ ሲሆን ነጻ፣ ሚስጥራዊ የልጆች እንክብካቤ ሪፈራል አገልግሎት ነው። ቤተሰቦች ኦንላይን ላይ መፈለግ ወይም በስልክ፣ በጽሑፍ ወይም በኢሜል የግል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

የሜሪላንድ የልጆች ጤና ፕሮግራም (MCHP)
የሜሪላንድ የልጆች ጤና ፕሮግራም (MCHP) ቤተሰቦቻቸው Medicaid ለማግኘት የሚሆን በቂ ገንዘብ የሚያገኙ ነገር ግን ገቢያቸው የግል የጤና መድህን ለመግዛት በቂ ያልሆነላቸው እና ብቁ ለሆኑ ኢንሹራንስ ለሌላቸው ልጆች ነጻ ሽፋን ይሰጣል። ምንም እንኳን እርስዎ ብቁ ባይሆኑም ልጅዎ ለMedicaid ወይም ለMCHP ብቁ ሊሆን ይችላል።
ለሜሪላንድ የልጆች ጤና ፕሮግራም ብቁ ለመሆን፣ አንድ ህጻን የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፥
- የሜሪላንድ ኑዋሪ መሆን።
- የአሜሪካ ዜጋ መሆን ወይም ዜጋ ያልሆነ ብቁ ሰው መሆን - የኢሚግሬሽን ሁኔታ መስፈርቶችን እና ልዩ ሁኔታዎችን ይመልከቱ።
- ከ19 ዓመት በታች መሆን።
- ሌላ የጤና መድህን የሌለው መሆን።
- የቤተሰብዎ መጠን የገቢ ገደብ ማሟላት።
- የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ይስጡ ወይም ለማህበራዊ ዋስትና ቁጥር ያመልክቱ።
በዚህ ገጽ ላይ የቀረቡት ሀብቶች የሁሉንም ነገር ዝርዝር የያዙ አይደሉም። ወደፊት ተጨማሪ ሀብቶች ይጨመራሉ። ምንም አይነት ጥያቄ ካለዎት እባክዎ እኛንያነጋግሩን።
ልጆችን እና ቤተሰቦችን ለመደገፍ የሚረዱ ሀብቶች
Thrive By 5 MoCo ከውልደት እስከ 5 ዓመት እድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች ለእነርሱ የሚሆኑ ሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን በቀላሉ መረዳት እንዲችሉ፣ መፈለግ እንዲችሉ እና መጠቀም እንዲችሉ ለመርዳት የተፈጠረ ማዕከላዊ የግብዓት/ሀብት ማዕከል ነው። ሀብቶች በአንድ ወይም ከዚያ በላይ ምድቦች ይከፈላሉ።
የልጆች እንክብካቤ እና ቅድመ-K
ትክክለኛውን የቅድመ ትምህርት ፕሮግራም ማግኘት በልጅዎ እድገት ውስጥ ወሳኝ እርምጃ ነው። እነዚህ ሀብቶች አዲስ ከተወለዱ ህጻናት እስከ ቅድመ-K ድረስ ለሚሆኑ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ስለሚገኙ አዲስ የልጆች እንክብካቤ እና የቅድመ-K አማራጮች መረጃዎችን ይይዛሉ። የተለያዩ የፕሮግራም ዓይነቶችን ለመፈለግ፣ የብቁነት መስፈርቶችን ለመረዳት፣ ያሉዎትን አማራጮች ለማነጻጸር እና ቅድመ እንክብካቤ እና ትምህርትን የበለጠ ተመጣጣኝ ለማድረግ ስለሚረዱ የገንዘብ ድጋፎች ለመማር የሚረዱ ሀብቶችን ያገኛሉ።
የቤተሰብ ድጋፎች
ትንሽ ልጅን ማሳደግ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስከትል ሲሆን፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ የተለያዩ ፍላጎቶች አሉት። እነዚህ ሀብቶች ከልጆች እንክብካቤ ባለፈ ልጆችን እና ተንከባካቢዎችን ከሚደግፉ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጋር ያገናኙዎታል። እየፈለጉ ያለው የልጅ አስተዳደግ ትምህርት ይሁን፣ የእድገት ድጋፎችን ይሁን፣ ቅድመ ጣልቃ ገብነትን ይሁን፣ ቤተ-መጻሕፍትን፣ የጨዋታ ቡድኖችን፣ የቤት ጉብኝት ይሁን ወይም ሌሎች የማህበረሰብ ሀብቶችን ቢሆንነ፣ እነዚህ ፕሮግራሞች ቤተሰብዎ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት እንዲበለጽግ እንዲረዱ ሆነው የተነደፉ ናቸው።
የገንዘብ ድጋፍ
ከፍተኛ ጥራት ያለው የቅድመ እንክብካቤ እና ትምህርት ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ተደራሽ መሆን አለበት። እነዚህ ሀብቶች የልጆች እንክብካቤ፣ የቅድመ--K፣ የጤና እንክብካቤ፣ የስነ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን ወጪ ለመቀነስ የሚረዱ ስኮላርሺፖችን፣ ድጎማዎችን እና ሌሎች የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራሞችን ይይዛሉ። ከዚህም ሌላ የብቁነት መስፈርቶችን ለመረዳት እና ለሚኖሩ ድጋፎች ለማመልከት የሚረዱዎትን ሀብቶች ያገኛሉ።
የጤና አገልግሎቶች
ጤናማ የሆኑ ልጆች በተሻለ ለመማር፣ ለማደግ እና ለበልጸግ ይችላሉ። እነዚህ ሀብቶች ቤተሰቦችን ከእርግዝና እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ድረስ ያሉ የልጆች ከሚደግፉ የጤና እንክብካቤ ሀብቶች ጋር የሚያገናኙ ሲሆን፣ እነዚህም የጤና መድህን ፕሮግራሞች፣ የልጆች እንክብካቤ፣ የቅድመ ወሊድ እና የድህረ ወሊድ አገልግሎቶች፣ የእድገት ምርመራዎች፣ የቤት ውስጥ ጉብኝት ፕሮግራሞች እና ሌሎች ከጤና ጋር የተያያዙ ድጋፎችን ያጠቃልላሉ። እርስዎ እየፈለጉ ያለው የመከላከያ እንክብካቤ ይሁን ወይም ልዩ አገልግሎቶችን፣ እነዚህ ሀብቶች የቤተሰብዎን ጤና እና ደህንነት ለመደገፍ ሊረዱ ይችላሉ።
የቅርብ ጊዜ መረጃዎችን ያግኙ
ለቤተሰቦች የበለጠ ጠቃሚ መረጃዎችን በመጨመር ይህንን ድህረ ገጽ በየጊዜው ወቅታዊ እናደርገዋለን። አዳዲስ መሳሪያዎች ሲኖሩ ማሳወቂያ እንዲደርስዎት ይመዝገቡ።